የሀገር ውስጥ ዜና

የገንዘብ ሚኒስትሩ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

February 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ አምባሳደር መሃመድ አብዲ አፌ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃገራት ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ እያከናወነች ያለውን ተግባር በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የሰብአዊ ድጋፍ መልሶ ግንባታ በተመለከተም ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው መንግስት እያደረገ ያለውን ሰብአዊ ድጋፍ እንዲሁም የስደተኞችን ደህንነት ከመጠበቅ አኳያ መንግስት የወሰዳቸውን እርምጃዎችን አድንቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!