Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ድል በመላው ኢትዮጵያውያን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትግል የተገኘ የአፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝቦች ድል ነው – ወ/ሮ ሎሚ በዶ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በክልሉ  ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅት በመላው ኢትዮጵያውያን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትግል የተገኘ የአፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝቦች ድል ለሆነው 125ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የክልሉ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በክልሉ የተከናወኑ ስራዎችን  መገምገሙን ወይዘሮ ሎሚ ተናግረዋል።

በዚህም 16 ዞኖች ፣ በ40 ወረዳና ከተሞች እንዲሁም በ80 ቀበሌዎች ያለው የስራ እንቅስቃሴ የመስክ ጉብኝትመደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ወቅት በየአካባቢው ያለው የልማት ስራዎች፣ ፕሮጀክቶች፣ የፍትህ ሂደት ስርዓት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ መሳሰሉት መታየታቸውንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ባለፈም በክልሉ ከ120 ሺህ በላይ ከሚሆኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት  መደረጉንም ጠቁመዋል።

አፈ ጉባኤዋ ጨፌ ኦሮሚያ በህገመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ እየተወጣ እንደሚገኝም ነው የገለጹት።

በተጨማሪም በዚህ ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ ከሚሰራባቸው ጉዳዮች ውስጥ ስድስተኛው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ  እንደሚሰራ ጠቅሰው ከህብረተሰቡም ትልቅ ስራ ይጠበቃል ብለዋል።

አፈ ጉባኤዋ አያይዘውም ህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ተወካዮቹን ከመምረጥ ባለፈ ምርጫው ተዓማኒ፣ ነጻና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን መሪ ተዋናይ መሆን አለበትም ነው ያሉት።

የጨፌ ኦሮሚያም ምርጫው የተሳካ እንዲሆን የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እንደሚወጣም መግለጻቸውን ከጨፌ ኦሮሚያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.