የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ድጋፍ ሁኔታ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተናገሩ

By Tibebu Kebede

February 25, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤዝሊ በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ድጋፍ ሁኔታ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ዳይሬክተሩ በትግራይ ክልል ካለው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ቡድን ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም አሁን ላይ በክልሉ ያለው ሰብአዊ ድጋፍ ሁኔታ መሻሻል አሳይቷል ነው ያሉት፡፡

ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን ተጨማሪ ገንዘብ እና ስራዎች እንደሚያስፈልጉ ጠቅሰዋል፡፡

አያይዘውም በክልሉ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!