Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ኮቪድ 19ኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራዋን ያስቀጠለችበትን ተሞክሮ ለዓለም አቀፉ የትምህርት ውይይት መድረክ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የትምህር ውይይት ላይ ተሳትፋለች።
በመድረኩ የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ወቅት የመማር ማስተማር ስራውን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቶች ዳግም ሲከፈቱም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶች የሚተገበር የኮቪድ መከላከል ፕሮቶኮል በማዘጋጀት፣ ማህበረሰቡን ያሳተፈ “ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ” ንቅናቄን በማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ማስቀጠሏን አብራርተዋል።
የተለያዩ ሀገራትም ዳግም ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት ሲገደዱ ኢትዮጵያ ማህበረሰቡን ባሳተፈ ስራዋ ውጤታማ ስራ መስራቷ በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡
በውይይቱ የትምህርት ዘርፍ የሰው ሃይል ልማት፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች፣ ለሴቶችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ትምህርትን በፍትሃዊነት ማዳረስ ላይም መምከራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.