የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት ሰባት ወራት ከ169 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

By Tibebu Kebede

February 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ሰባት ወራት 169 ቢሊየን 501 ሚሊየን 789 ሺህ 893 ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

አፈፃጸሙ ከዕቅድም ሆነ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ የታየበት መሆኑን ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ 169 ቢሊየን ብር 408 ሚሊየን 889 ሺህ 4 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የእቅዱን 100 ነጥብ 5 በመቶ ማሳካት መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!