የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴራል እና የደቡብ ክልል የስራ ኃላፊዎች በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶርዜ ከተማ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

By Meseret Awoke

February 26, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴራል እና የደቡብ ክልል የስራ ኃላፊዎች በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶርዜ ከተማ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ፣ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

ለልኡካን ቡድኑ የሰላም አምባሳደር የሆኑት የጋሞ አባቶች እርጥብ ሳር በመያዝ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!