Fana: At a Speed of Life!

እነ ስብሃት ነጋ እና አባይ ወልዱ  ጨምሮ ለ4ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ፖሊስ የተሳትፎ ደረጃቸውን ለይቶ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ አዘዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)እነ ስብሃት ነጋ እና አባይ ወልዱ  ጨምሮ ለ4ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ፖሊስ የተሳትፎ ደረጃቸውን ለይቶ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ አዘዘ።

ተጠርጣሪዎቹ ለ4 ኛ ጊዜ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው እየታየ ነው።

መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ  በመቀሌ ያለው ምርመራ ቡድን የ85  ሰዎች ምስክር ቃል ተቀብሎ መላኩን  500  ገጽ የሰነድ ማስረጃ ማስተርጎሙን እና 200 የምስክር ሰነድ ማደራጀቱን አብራርቷል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች መነሻ መጠርጠሪያ ሳይኖር ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ አይደለም ሲሉ መከራከሪያ ነጥብ አንስተዋል።

ተሳትፏቸው አልተለየም ሲሉ ም  ጠበቆቹ መቃወሚያ አሰምተዋል።

ፖሊስ የሰበሰባቸውን ሰነዶች አስተርጉሞ ለይቶ እንዲቀርብ ያዘዘው ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርመራ 13 ቀን ለፖሊስ ፈቅዷል።

አቶ ስብሃት በግል ሀኪም እንዲታከሙ ያቀረቡትን  አቤቱታም በተመለከተ ፍርድ ቤቱ የግል ሀኪማቸው ባሉበት እስርቤት መጥተው  ህክምና እንዲሰጣቸው የፈቀደ ሲሆን ÷ ከፍ ባለ የህክምና መሳሪያ መታገዝ ካለባቸው አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ  ብሏል።

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.