Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተናን በልዩ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ ኢንጅነር አስቴር ይትባረክ ዛሬ እንዳስታወቁት በክልሉ 12ሺህ ያህል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ይገኛሉ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የሚሰጠው 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች በትግራይ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ተገኝተው ፈተና እንዲወስዱ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

ተማሪዎቹ በመቀሌ፣ አክሱም፣ በአድግራትና ራያ ዩኒቨርስቲዎች እስከ የካቲት 23 ቀን 2013ዓ.ም. ድረስ በአካል ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪ ማድረጉን ገልጸዋል።

ባለፉት ወራት የመማር ማስተማር ሂደት ባይኖርም ተማሪዎች ቀደም ባሉት ዓመታት የትምህርት ዝግጅት እያደረጉ በመምጣታቸው 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንዲቀመጡ ያስችላችዋል ብለዋል።

ተማሪዎቹ ቀደመው በዩኒቨርሲቲዎቹ በመገኘት ለአስር ቀናት ያህል ዝግጅት እንዲያደርጉ እድል መሰጠቱን ኢንጅነር አስቴር አስታውቀዋል።

ተማሪዎች በዚህ እድል ተጠቅመው ፈተናውን በወቅቱ እንዲወስዱ መምህራንና ወላጆች በመደገፍ ትብብር እንዲያደርጉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በክልሉ ከህግ ማስከበሩ ጋር ተያይዞ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ያስከተለውን መስተጓጎል ግምት ውስጥ ያስገባ ምዘና እንዲደረግም ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚወያይ ኢንጅነር አስቴር መግለጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.