Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ከአራት ሺህ አንድ መቶ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን ከአራት ሺህ አንድ መቶ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ዩኒቨርስቲው በ65ኛ ዙር  ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ከዛሬ ስድሳ ስምንት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ መንግስትና በአሜሪካን ኦክልሃማከ ስቴት ዩኒቨርስቲ አማካኝነት በግብርና ኮሌጅነት የተቋቋመው የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ዘንድሮ ለ65ኛ ጊዜ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን አራት ሺህ አንድ መቶ ሰባ አራት  ተማሪዎችን ነው ከመጀመሪያ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ያስመረቀው።

በሃምሳ ሁለት የትምህርት ፕሮግራሞች  3430ዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ፣385ቱ በ66 የትምህርት ፕሮግራሞች በድህረ ምረቃ እና 21ዱ በዶክትሬት ዲግሪ ነው የተመረቁት።

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ባለፉት ስድሳ አምስት ዓመታት ከ110 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቆ ወደ ስራ ማሰማራቱን በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

በተሾመ ኃይሉ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.