Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 1 ሺህ 516 የፖሊስ አባላትን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ አካዳሚ በ22ኛ እና በ23ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 516 መደበኛ የፖሊስ አባላትን አስመረቀ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለፖሊስ አባላቱ የስራ መመሪያ በመስጠት ወደ ስራ አሰማርተዋል ።

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት እና መላው የፀጥታው አካል ለከተማዋ ሰላም እና ፀጥታ መረጋጋት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ሊመሰገኑ ብለዋል ።

ፖሊስ የህብረተሰቡን ሰላም በመጠበቅ ፣ የከተማዋን ጸጥታ እና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት ከሰው ሀይል ጀምሮ በግብዓት እና በሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግም ገልጸዋል ።

የዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም እንዲካሄድ ፖሊስ እና መላው የፀጥታ አካል ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት አጠቀላይ ሊሰሩ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በከተማዋ ሀይማኖታዊ፣ ብሄራዊ እና ሌሎች ዝግጅቶች ካለምንም የጸጥታ ችግሮች እንዲከበሩኮሚሽኑ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አበረታች ስራዎች መሰራቱን ተናግረዋል።

በቀጣይም የከተማዋ ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን ተጨማሪ 60 ፖሊስ ጣቢያዎችን የማደራጀት ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል ።

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የማርቺንግ ባንድ ማስመረቁን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.