Fana: At a Speed of Life!

የባይደን የ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ዶላር የኮቪድ19 ማገገሚያ ረቂቅ በተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ያቀረቡትን የኮቪድ19 ማገገሚያ ረቂቅ እቅድን አፀደቀ፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኮሮና ቫይረስ ያደረሰውን ተፅዕኖ መቋቋሚያ ይሆን ዘንድ የ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ዶላር የማገገሚያ ረቂቅ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ምክር ቤቱም የፕሬዚዳንቱን እቅድ ያጸደቀው ሲሆን፥ ተግባራዊ ይሆን ዘንድም የሴኔቱ ይሁንታ ይቀረዋል፡፡

የእርሳቸው ረቂቅ እቅድ ለኮሮና ቫይረስ የሚደረገውን ምርመራ ማሳደግ፣ ለክትባት ተጨማሪ ወጪን ማድረግና በቫይረሱ ሳቢያ የተጎዳውን ኢኮኖሚ በስራ እድል ፈጠራ ማገዝን አላማው ያደረገ ነው፡፡

በዚህም ለነዋሪዎች ድጎማ ማድረግና አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መደገፍም የረቂቁ አላማ ነው፡፡

ባይደንም እቅዱ በኮቪድ19 ምክንያት ክፉኛ በተጎዳው የሃገሪቱ ኢኮኖሚ አሜሪካውያንን የሚያግዝ ነው ብለውታል፡፡

በአንጻሩ የፕሬዚዳንቱ ረቂቅ እቅድ በጣም የተለጠጠና የታጨቀ እንዲሁም ከወረርሽኙ ጋር ግንኙነት ለሌላቸው የዴሞክራቶች ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጥ ነው በሚል በሪፐብሊካን አባላት ዘንድ ተቃውሞን እያስተናገደ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.