የሀገር ውስጥ ዜና

የእጩዎች ምዝገባ ለአራት ቀናት ተራዘመ

By Tibebu Kebede

February 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢተዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ ለአራት ቀናት መራዘሙን አስታወቀ፡፡

ቦርዱ የመጀመሪያ ዙር የእጩ ምዝገባ የሚከናውንባቸው ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ማለትም

• የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር

• የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር

• የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል

• የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል

• የጋምቤላ ብሔራዊ ክልል

• ሃሪሪ ብሔራዊ ክልል ለእጩዎች ምዝገባ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት የካቲት 8 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ማሳወቁ ይታወሳል።

ሆኖም ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባ ሂደትን በመገምገም የምርጫ ክልል ቢሮዎች ለመከፈት በመዘግየታቸው፣ የትራንስፓርት መጓተት የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ የምዝገባ ቀንን በማራዘሙ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች እጩዎችን ለመመዝገብ ችግር ስላጋጠመን ይራዘምልን ብለው መጠየቃቸውን ገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ በጀመሩት ክልሎች/የከተማ መስተዳድሮች ላይ የሚካሄደው የእጩዎች ምዝገባ ለአራት ቀናት ያህል እስከ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!