የሀገር ውስጥ ዜና

የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ተደራሽ ለማድረግ አመራሩ የበኩሉን ሊያበረክት እንደሚገባ ተገለፀ

By Meseret Awoke

February 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማህበረሰብ አቀፍ የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ በድሬዳዋ ከተማ ተካሄደ ፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ የማህበረሰብ አቀፍ የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደረግ በመሆኑ ሁሉም ማህበረሰብ በጤናና አካል በቃት እንቅስቃሴ ስፖርት መሳተፍ አለበት ብለዋል፡፡

በድሬደዋ ከተማ በተካሄደው 3ኛው ሀገር አቀፍ የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ፣ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጆሃርን ጨምሮ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ፣ አካል ጉዳተኞችን ፣ ህፃናት እንዲሁም በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!