የሀገር ውስጥ ዜና

“እኔም ለደሴ እሮጣለሁ” ሕዝባዊ ሩጫ በደሴ ከተማ ተካሄደ

By Meseret Awoke

February 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ለመደገፍ “እኔም ለደሴ እሮጣለሁ” በሚል መሪ ቃል ሕዝባዊ ሩጫ በደሴ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማኅበር ባዘጋጀው ሕዝባዊ ሩጫ ላይ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎችና ከተለያዩ አካባቢዎች የታደሙ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ክለቡን ለማገዝ ከ4ሺህ በላይ ቲሸርቶች ታትመው ለሽያጭ መቅረባቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

የደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እየተወዳደረ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ዓመት በሊጉ በመጀመሪያው ዙር ውድድር በምድብ አንድ በ16 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!