Fana: At a Speed of Life!

የ2013 የኢትዮጵያ ክልሎችና ክለቦች ውሃ ስፖርቶች ሻምፒዮና መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ክልሎችና ክለቦች ውሃ ስፖርቶች ሻምፒዮና በኮምቦልቻ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ሻምፒዮናው በኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን አዘጋጅነትና በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስተናጋጅነት በኮምቦልቻ ከተማ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ ሶርሳ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው ለዚህ ዓመታዊ ሻምፒዮና በመብቃታችን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡
ይህ የሻምፒዮና ውድድር በኮቪድ 19 ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን ስፖርት መልሶ ለማነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በውሃ ስፖርቶች ተተኪ እና ምርጥ አትሌቶችን ለማፍራት እንደነዚህ አይነት ውድድሮች ወሣኝ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገርን ስም የሚያስጠሩ ምርጥ ስፖርተኞችን ለማፍራት ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ስለሆነም ሁሉም ባለድርሻ አካል ለስፖርቱ እድገት እና መስፋፋት በመተባበርና በቅንነት መስራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ሻምፒዮናውን ወንድማማችነትን፣ አብሮነትነን ፣ መተሳሰብንና አንድነትን ለመፍጠር መድረኩን ልንጠቀምበት ይገባል ማለታቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሻምፒዮናው ዛሬ በተለያዩ የውድድር አይነቶች የፍፃሜና የማጣሪያ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን አመታዊው ሻምፒዮናው እስከ የካቲት 27 እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.