የሀገር ውስጥ ዜና

125ኛውን የአድዋ ድል በዓል የሚዘክር የባሕል ኮንሰርት በወዳጅነት አደባባይ ተካሄደ

By Tibebu Kebede

February 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል የሚዘክር የባሕል ኮንሰርት በወዳጅነት አደባባይ ተካሄደ።

125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

ከዝግጅቶቹ መካከል አንዱ የድል በዓሉን የሚዘክር የባሕል ኮንሰርት በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል።

በኮንሰርቱ ላይ በመገኘት የዕለቱን መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዲሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሳው 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል የምናከብረው፤ ዓድዋ የኢትዮጵያውያን ልዕልና ስለሆነ ነው ብለዋል።

በዚህ የአድዋ ኮንሰርት ወጣቶች፣ ሴቶችና ሕጻናት እንዲሳተፉ የተደረገው የነገ ሀገር ተረካቢ፣ ታሪክ አስተላላፊ እና ድርብ ኃላፊነት ያለባቸው ስለሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል።