Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከቀነሰ የተቀመጡ ገደቦችን እንደምታላላ አስታወቀች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከቀነሰ የተቀመጡ ገደቦችን እንደምታላላ አስታወቀች፡፡

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተቀመጡ እገዳዎች ከደረጃ ሶስት ጀምሮ እስከ አንድ እንደሚወርድ አስታውቀዋል፡፡

ራማፎሳ በበዓል ወቅት የተቀመጡት ገደቦች የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ እንዳገዙና የተሳኩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ራማፎሳ አሁን የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ሁሉም ጉልበትና ጥረት ኢኮኖሚን ለማሳደግ መሆን እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

የሶስተኛ ዙር የቫይረሱ ስርጭት ሥጋት እንዳለ የገለፁት ፕሬዚደንቱ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ፣ ህዝብ ከተሰበሰበበት ቦታ መራቅ እና ጭምብል ማድረግ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል ፡፡

አሁን ላይ በሃገሪቱ 1ሚሊየን 513 ሺህ 393 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ዚሆን 49 ሺህ 993 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.