የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመሆን ተሾሙ

By Abrham Fekede

March 01, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር አህመድ ሙስጠፋ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አድርጎ መሾሙን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በቅርቡ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ዩኒቨርሲቲውን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት ለሚፈልጉ ሁሉ በመገናኛ ብዙኀን ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ስምንት ተወዳደሪዎች ቀርበው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ከተወዳዳሪዎቹ መካከልም ዶክተር አህመድ የዩኒቨርሲቲውን ሴኔት ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት ነው ቀጣዩ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት፡፡

ሚኒስቴሩ ከፍተኛ አደራና ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን በማሳሰብ ኃላፊነታቸውን በትጋት እንዲወጡም አሳስቧል፡፡

ዶክተር አህመድ ላለፉት ሁለት ዓመታት ዩኒቨርሲቲውን በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንትነት ኋላም ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት 14 ዓመታት  ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!