Fana: At a Speed of Life!

የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው።
 
በበዓሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ ከአጎራባች የተገኙ በርካታ እንግዶችና የተለያዩ ብሔር ተወላጆች ተገኝተዋል።
 
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ በስነ ስረዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የሴራ ባህል ተጠብቆ ለሚመጣው ትውልድ ሊተላለፍ እንደሚገባ አውስተዋል።
ከልማት ስራዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በቀጣይ የሚሰራ መሆኑም አብራርተዋል።
 
የዞኑ ዋና አስተዳደር ዶክተር መሃመድ ኑሪዬ በበኩላቸው፥ የሴራን ባህል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በተሻለ መልኩ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን ዛሬ ጠዋት የልማት ስራዎችን የመመረቅና የዞን መስተዳድር ተቋም ግምባታ የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ዝግጅት ተከናውኗል።
 
በትናንትናው ዕለት ደግሞ የሀላባ የመጀመሪያው የባህልና እሴቶች ጥናት ሲምፖዚዬም መካሄዱ ተመላክቷል።
 
በብርሃኑ በጋሻው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.