የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል ለ54 ከተሞች ሽግግር ተፈቀደ

By Meseret Awoke

March 01, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከተሞችን የእድገት ማዕከል ለማድረግ ለ54 ከተሞች ሽግግር መፈቀዱን የአማራ ክልል ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ ገለጸ።

በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ደረጃ የአማራ ክልል ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሰዒድ ኑሩ እንደገለጹት፤ ከተሞችን የብልጽግና ማዕከል ማድረግ አንደኛው ሥራ ነው፡፡

በከተሞች ሀብት መፍጠር፣ ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑና የስልጣኔ ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለ54 ከተሞች ሽግግር መፈቀዱን የጠቀሱት ዶክተር ሰኢድ የክልሉ መንግሥት ቢሮው ያቀረበለትን ጥያቄ መቀበሉን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ ሂደትም ለታዳጊ ከተማነት ከገጠር ማዕከል 10፣ ከታዳጊ ከተሞች ወደ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት 10፣ ከንዑስ ማዘጋጃ ቤት ወደ መሪ ማዘጋጃ ቤት አራት እና ከመሪ ማዘጋጃ ወደ ከተማ አስተዳደርነት 30 ከተሞች መሸጋገራቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!