የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

March 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሴቶች ወር አከባበርን በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ እና ታዋቂ ከሆኑ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር በመወያየት ጀምረውታል፡፡

ስኬታማ ሴቶች በኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣት ሴቶችን በመደገፍና በማበረታታት ረገድ ቁልፍ ሚና እንዳላቸው በዚህ ወቅት ተነስቷል፡፡

ተሳታፊዎቹም በፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ በተጀመሩ የተለያዩ መርሀ ግብሮች ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የዜቶች ወር በመጪው ወር ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ተጨባጭ የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማፍለቅ ታቅዶ የተጀመረ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!