Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ድል ነጻነታችንን ያወጅንበት እና ታላቅ ተጋድሎ ያደረግንበት ታሪካዊ ክስተት ነው – አቶ እርስቱ ይርዳ  

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት የድል አርማ የሆነው የአድዋ ድል ነጻነት የታወጀበት እና ታላቅ ተጋድሎ የተደረገበት ታሪካዊ ክስተት ነው አሉ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት 125ኛውን የአድዋ ድል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ነው፡፡

አባቶች የጠላት ወረራን ለመመከት ዘር፣ ቀለምና ሃይማኖት ሳይለዩ፣ ሳይከፋፈሉ በአንድ ሀገራዊ ስሜት ዘመናዊ መሳሪያን ሳይሆን የጀግንነትና የአትንኩኝ ባይነት ስሜት አንግበው ጋራ ሸንተረሩን አቋርጠው ታላቅ ተጋድሎ አድርገው ለዚህ አብቅተውናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የአድዋ ድል “የእኛ የኢትዮጵያውያን ድል ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካውያን ድል ነው” መሆኑን ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ያስረዱት፡፡

ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ስናከብር በድህነት ላይ የጀመርነውን ትግል በማጠናከር ሊሆን ይገባልም ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ዛሬም አንድነትንና አብሮነትን በማጠናከር የብሔር እና የሀይማኖት ልዩነቶችን በመቻቻል እና በመከባበር ብሎም በወንድማማችነት መንፈስ ማስተናገድ እንደሚገባም ነው የጠቀሱት፡፡

የአሁኑ ትውልድም የጥንት ጀግኖች አባቶችን የሀገር ፍቅር ስሜት በመያዝ ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከርና ለእድገቷም መትጋት ሊተጋ እንደሚገባ አስታውሰዋል፡፡

ሀገርን ከወራሪ ጠላት ከመጠበቅ በተጓዳኝ “ዛሬ አንድነታችን ያላስደሰታቸው አካላት በየጊዜው አዳዲስ አጀንዳዎችንና ሀሰተኛ መረጃዎችን እየቀረጹ ሊከፋፍሉን ይፈልጋሉ ይህ ምኞታቸው ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም፣ መላው የሀገራችን ወጣቶች ይህንን ታግሎ ማሸነፍ ይጠበቅባችኋል” ሲሉ አሳስበዋል ፡፡

በተለይ ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ ጠንክሮ በመስራት ድህነትን ታሪክ የሚያደርግበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ከፊት ለፊታችን ብሩህ ተስፋ እንዳለ በመገንዘብ  የሀገራችንን ህዳሴ ወደ ከፍታ ምዕራፍ ማሻገር የዚህ ትውልድ የቤት ስራ ነው ሲሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.