የሀገር ውስጥ ዜና

125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

By Abrham Fekede

March 02, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች የተከበረው 125ኛው የአድዋ የድል በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ምኒልክ አደባባይ በተመሳሳይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የተከበረው እና የድል በዓሉን አስመልክቶ መነሻውን  ምኒልክ  አደባባይ መዳረሻውን አድዋ ድልድይ የተደረገው የእግር ጉዞ በደማቅ ሁኔታ በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

125ኛው የአድዋ የድል በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ህብረተሰቡ ላደረው ቀና ትብብር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ኮሚሽኑ ምስጋናውን ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!