Fana: At a Speed of Life!

በጉራጌ እንደባህል የሚጠቀሰው ስራ ወዳድነት ለሁሉም እሴት መሆን የሚችል ነው-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጉራጌ እንደባህል የሚጠቀሰው ስራ ወዳድነት ለሁሉም እሴት መሆን የሚችል ነው፣ አዲስ አበባ ደግሞ ብዙ የሚለፉ እጆችን ትፈልጋለች ሲሉ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ ይህንን የተናገሩት  የደቡብ ብሔር ብሔርሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ እርስቱ ይርዳውና የቦርድ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት በጉራጌ ልማት ማህበር ዓመታዊ ኮንፍረንስ ላይ ተገኝተው ተገኝተው ነው።

ሀገርን ለማልማትና ለመለወጥ  ትብብር እና መከባበር እንዲሁም ዝቅ ብሎ መስራትና መድከም ይጠይቃል  ሲሉ ወይዘሮ አዳነች ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ  እንድትበለጽግ የማህበሩ አባላት በግልም ሆነ በጋራ ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ÷ አብረን ተባብረን የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ባደግንባቸውና በመራንባቸው ከተሞች ሁሉ ጉራጌዎችን የምናውቃቸው የልማት ኮሚቴ ሆነው ከተሞችን ሲያለሙ ነው ሲሉ ተናግረዋል

ወይዘሮ አዳነች  አያይዘውም ማህበሩን ለማልማት በምታደርጉት ጥረት ሁሉ የከተማ አስተዳደርሩ ከጎናችሁ ነው ብለዋል፡፡

በግልም የልማት ማህበሩ አባል ለመሆን ያላቸውን ፍላጎት  ከንቲባዋ መግለጻቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.