መቄዶንያ በጎሬ ከተማ ያቋቋው ማዕከል ተመርቆ ስራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በጎሬ ከተማ ያቋቋመው ቅርንጫፍ ተመርቆ በይፋ ስራ ጀመረ።
የማዕከሉ ተወካይ አቶ ራጂ አማና በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ እንደገለጹት ÷ማዕከሉ ከአዲስ አበባ ውጭ ያቋቋመው 3ኛው ቅርንጫፍ በጎሬ ከተማ 100 የሚሆኑ አቅመ ደካማ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማንን ተቀብሎ ድጋፍና እንክብካቤ ያደርጋል።
ማዕከሉ የገቢ አቅሙን ለማጠናከር በጎሬ ከተማ አገልገሎት መስጫ ተቋማትን የማቋቋም እቅድ እንዳው ጠቁመው÷ የከተማው አስተዳደር ማዕከሉ ለሚያከናውናቸው ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በጎሬ የተቋቋመው ማዕከል በማሻና ጋምቤላ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው የሚገኙ አረጋውያንንና የአእምሮ ህሙማንን ከጎዳና በማንሳት የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት እንደሚሰጥ አመላክተዋል።
ማዕከሉ ከዘጠኝ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ 40 አቅመ-ደካማ አረጋውያንን ከጎዳና በማንሳት የበጎ አድራጎት ሥራውን መጀመሩን አስታውሰው፤ ቅርንጫፎቹን በክልል ከተሞች እያስፋፋ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሜቄዶንያ ጎሬ የቅርጫፍ ማዕከል ምረቃ ስነ ስርአት ላይ የማዕከሉ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ኢሌኒ ገብረየሱስን ጨምሮ፣ የኢሉ አባቦር ዞንና የጎሬ ከተማ አስተዳደር አካላትና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!