የሀገር ውስጥ ዜና

የስፔስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የግብርና ምርት ውጤታማነትን ማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

By Meseret Awoke

March 03, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የስፔስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የግብርና ምርት ውጤታማነትን ማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል::

ስምምነቱ የሳተላይት መረጃን ተጠቅሞ ግብርናን ለማዘመን ፤ በአየር ንብረት ቅድመ ትንበያ እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በስምምነቱ ወቅት በ15 ቀናት ዉስጥ ቡድን ተቋቁሞ ወደ ተግባር እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን፥ ግብርናን ለማዘመን ባለሙያዎችን ማሰልጠን ወሳኝ መሆኑም ተነስቷል፡፡

ከስምምነቱ ባለፈ በፍጥነት ወደ ተግባር ተገብቶ ግብርናን ማዘመን እንደሚገባ የጋራ መግባባት መፈጠሩን ከኢንስቲቲዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግና