Fana: At a Speed of Life!

በ170 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በ170 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው በልዮ ዘመቻዎች ኃይል ስር የሚገኘው የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ህንጻ የመሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በልዮ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ስር በሚገኘው የአየር ወለድ ትምህርት ቤት ህንጻ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ በቢሾፍቱ አየር ኃይል ጊቢ ውስጥ አስቀምጠዋል።

የሚገነባው ህንጻ የትምህርት ቤቱን አቅም ለማጠናከር የሚያገለግል መሆኑ ታውቋል።

ህንጻው በአንድ አመት ውስጥ ተሰርቶ እንደሚጠናቀቅ ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም አጠቃላይ የአየር ወለድ የስልጠና ሂደት ጉብኝት የተደረገ ሲሆን፤ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ የአየር ወለድ ዝላይና የተኩስ ትርኢት መካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.