የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል

By Tibebu Kebede

March 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል፡፡

በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርግ በምክር ቤቱ የፕሬስና ህዝብ ግነኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ አለም እንቻለው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩን ፍርድ ቤቶች የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የሚገመግም ሲሆን ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!