የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከሴናተር ጂሚ ኢንሆፍ ጋር በትግራይ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

March 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሴናተር ጂሚ ኢንሆፍ ጋር በትግራይ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ተንቀሳቅሰው ድጋፍ እንዲያደርጉ መንግስት እየሰራ እንዳለ ገልጸዋል።

መንግስት በክልሉ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱ እንዲጠናከር በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ሴናተሩ አካባቢው ለዓለም አቀፍ ሰብአዊ ድጋፊ አቅራቢ ድርጅቶች ክፍት መደረጉ መልካም መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ክልሉ እንዲረጋጋ እና ግልጸኝነት እንዲኖር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት።

ሴናተር ጂሚ ኢንሆፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ለውጦችን እያስመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀጠናው እንዲረጋጋ እና ብልጽግና እንዲረጋገጥም መስራታቸውን እንደሚቀጥሉም ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ ብለዋል።

ሴናተሩ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርብ መወያየታቸውን እንደሚቀጥሉም አንስተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!