የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ምስጋና አቀረቡ

By Tibebu Kebede

March 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዴቪድ ቢስሊ ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዋና ስራ አስፈጻሚው በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት አስመልክቶ ላደረጉት ገንቢ አስተዋጽኦ እና ተጨባጭ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጰያ የሚያከናውነው ሥራ የሚደነቅ እና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!