የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

By Tibebu Kebede

March 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈጻሚ ዴቪድ ቤስሊ በትግራይ ክልል ድጋፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከተወያዩ በኋላ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ለድጋፉ 107 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡

በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ወዳጅ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!