Fana: At a Speed of Life!

የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ይፋ ተደርጓል።

የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ይፋ መደረግ ያስታወቁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው፡፡

አቶ ደመቀ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ፕሮግራሙ ከ2013 እስከ 2027 የሚተገበር ነው ብለዋል፡፡

የፕሮግራሙ መሻሻል ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝም ነው ያስታወቁት፡፡

ፕሮግራሙ ዘርፈ ብዙ ምላሽ የሚሰጥ በመሆኑ በየደረጃ ያለው አመራር መምራትና መደገፍ ይኖርበታል ሲሉም አሳስበዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም መሰረታዊ የጤና አገልግሎትን ለዜጎች ተደራሽ ከማድረግ እና ህብረተሰቡ በሽታን በመከላከል የራሱን ጤና ራሱ እንዲያመርት ግንዛቤ በመፍጠርና በማስተማር በተሰራው ስራ በተላላፊ በሽታዎች የሚከሰቱ ህመምና ሞት መቀነሱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የእናቶችና ህፃናትን ሞት በመቀነስ ኢትዮጵያ ላሳካቻቸው የምዕተ ዓመት የልማት ግቦች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷልም ነው ያሉት፡፡

ለዚህ ስኬት ዋና ተዋናይ ለሆኑትና በመስዋዕትነት ለሚያገለግሉት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አሁን የተዘጋጀው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምም እያደገ ላለው የህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ፍላጎት፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ጨምሮ የበሽታዎች ስርጭት መለዋወጥ፣ ከስነ-ህዝብ ለውጦችና እያደገ ካለው የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር በተጣጣመና መፍትሄን በሚሰጥ መልኩ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.