የሀገር ውስጥ ዜና

ከ5 ሺህ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ሁለት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ተዘዋውረዋል – የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ

By Tibebu Kebede

March 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ 5 ሺህ 844 ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሁለት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ማዛወሩን አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው በማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች 295 ተጨማሪ ስደተኞችን መቀበሉን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከሽሬ እና አካባቢው ወደ ጣቢያዎቹ የተዛወሩ ስደተኞች ቁጥር 5 ሺህ 844 ደርሷል ነው ያለው፡፡

ስደተኞችን ከማዛወር ጎን ለጎን የአስቸኳይ መጠለያ ግንባታ እየተፋጠነ እንደሚገኝም ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!