Fana: At a Speed of Life!

የሊቢያ ተቀናቃኝ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ለፈራረሙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሊቢያ ተቀናቃኝ ሀይሎች በሩሲያ ሞስኮ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈራረሙ ነው።

ስምምነቱን በተመድ ህጋዊ እውቅና ያለው የፋይዝ አል ሳራጅ አስተዳደር እና ተቀናቃኙ ጀኔራል ከሊፋ ሃፍታር በዛሬው እለት ይፈርሙታል ተብሎ ይጠበቃል።

ስምምነቱን ይፈርማሉ ከማለት ውጭ ግን የፊት ለፊት ውይይት ስለማድረግ አለማድረጋቸው የተባለ ነገር የለም።

ፋይዝ አል ሳራጅ በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ሊቢያውያን ያለፈው ገጽ እንዲዘጉ ጥሪ አቅርበዋል።

አያይዘውም ሁሉም ሊቢያውያን በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የሰላም ስምምነቱ መደረስ ለሃገሪቱ ፖለቲካዊ ቀውስ እልባት ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.