የሀገር ውስጥ ዜና

በዱከም ከተማ 3 ሺህ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የምግብ እህል ድጋፍ ተደረገ

By Tibebu Kebede

March 04, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና በዱከም ከተማ አስተባባሪነት ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች የምግብ እህል እና የንፅህና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ለነዋሪዎቹ ተንቀሳቃሽ ወንበር፣ የምግብ እህል፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ የምግብ ዘይት እና የእህል ወፍጮ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲምቢሩ ይህ ስራ ለዜጎች የዕለት ድጋፍ ከማቅረብ በዘለለ ሰርተው ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያድርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዱከም ከተማ ከንቲባ አቶ ተሾመ ግርማ ድጋፍን ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ነዋሪዎቹም ከተረጂነት በመውጣት ራሳቸውን የሚችሉበት ድጋፍ ስለተደረገላቸው አመስግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!