የሀገር ውስጥ ዜና

ለአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

By Abrham Fekede

March 04, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቋል፡፡

ይህ የተባለው አሁን እየተካሄደ በሚገኘው ዝክረ አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ነው፡፡

የሙዚቃ ኮንሰርቱ በሸገር ወዳጅነት ፓርክ ውስጥ ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው፡፡

ኮንሰርቱ “ቆሜ ልመርቅሽ” በሚል በአልበሙ መጠሪያ ነው የተሰየመው፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በአርቲስቱ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ህያው እንዲሆን ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

የመሰረት ድንጋዩ ከሸራተን ሆቴል ፊትለፊት እንደተቀመጠም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!