የሀገር ውስጥ ዜና

የአሜሪካ በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት አግባብነት የለውም- ሩሲያ

By Meseret Awoke

March 05, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ሩሲያ ጥሪ አቀረበች፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቡድን በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመዋል፡፡

ቡድኑ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆምም ጠይቀዋል።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቡድኑ የአጋሮችን ፍላጎት ከግምት ሳያስገባ እና ሳያከብር የሚወስነው ውሳኔ ተገቢ አለመሆኑን ነው ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የገለጹት።

ሩሲያ ከዚህ በፊትም ኢትዮጵያ ያካሄደችው የህግ ማስከበር ስራ እና አሁን ደግሞ የትግራይ ክልልን የመልሶ ማቋቋም ምዕራፍ የውስጥ ጉዳይ እንጂ የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚያሻው አለመሆኑን ደጋግማ ገልጻለች።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!