Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ሁለት ደንቦችን መርምሮ አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 226ኛ መደበኛ ሰብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ ከተቋማት በቀረቡለት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀም ለማሻሻል የሚያግዙ ጥያቄዎችን መርምሮ ማፅደቁን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የግብርና ምርቶች ግብይት ማዕከላት ግንባታና አስተዳደር ደንብ እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች የህዝበ ውሣኔ ማስፈጸሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ማቋቋሚያና የአሰራር ሥርዓት መወሰኛ ደንቦችን መርምሮ አጽድቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.