አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከርና ህግን በማክበር እና በማስከበር ሴቶች ያላቸዉ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሴት አሽከርካሪዎችና የትራፊክ ፖሊሶች በመንገድ ደህንነት ፣ በትራፊክ ህግ፣ አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር ፣ የትራፊክ አደጋ መንስኤዎች እና በማሽከርከር ስነ ምግባር ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም ብቻ 4 ሺህ 133 ዜጎች በትራፊክ አደጋ ምክንያት ሕይዎታቸውን ያጡ ሲሆን ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑት ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
9 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ደግሞ መውደሙ ተገልጿል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አደጋዉ እንዲቀንስ ትኩረት በመስጠት ህዝባዊ የመንገድ ደህንነት ንቅናቄዎች ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት የቁጥጥር ስራዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ እያደረገ መሆኑን አንስተዉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻዉን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ ሴቶች አደጋን ባለማድረስ፣ ተከላክሎ በማሽከርከር፣ ህግን በማክበር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸዉ ገልፀው ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!