Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የኮቪድ 19 ክትባት ልትረከብ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ኮቫክስ ከተሰኘው አለምአቀፍ ጥምረት 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የኮቪድ 19 ክትባት ልትረከብ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
መንግስት ክትባቱን የፊታችን እሁድ እንደሚረከብ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የጤና ሚኒስቴርም ክትባቱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የክትባት ፕሮግራሙም በቀጣዮቹ ሳምንታት ይፋ እንደሚደረግ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

 https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.