Fana: At a Speed of Life!

ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ መዘጋጀቱን ሚኒስቴሩ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ መዘጋጀቱን ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ እንደገለጸው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋው ከነገ የካቲት 27 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

በዚሁ መሰረት ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ ከተማ ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።

ቤንዚን በሊትር 25 ብር ከ 86 ሳንቲም፥ ኤታኖል ድብልቅ ቤንዚን በሊትር 25 ብር ከ 36 ሳንቲም፥ ነጭ ናፍጣ በሊትር 23 ብር ከ18 ሳንቲም፥
ኬሮሲን በሊትር 23 ብር ከ18 ሳንቲም፥ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 20 ብር ከ27 ሳንቲም፥ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 19 ብር ከ78 ሳንቲም፥
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 38 ብር ከ65 ሳንቲም ይሆናል ብሏል ሚኒስቴሩ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ በተመለከተ በዝርዝሩ የተካተቱ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫን ለማሳወቅ የህዝብ ማስታወቂያ በነገው ዕለት ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

በዚሁ መሰረት በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.