Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ ተቋርጦ የነበረውን ቤት ፈላጊዎችን የማደራጀት ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህርዳር ከተማ ተቋርጦ የነበረው ቤት ፈላጊዎችን የማደራጀት ስራ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ አማረ አለሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ከ2006 እስከ 2011 ዓ.ም ከ27 ሺህ በላይ ቤት ፈላጊዎች ቢደራጁም እስከ 2010 ድረስ ቤት አለማግኘታቸውን ምክትል ከንቲባው ጠቅሰዋል።

ባለፈው አመት 16 ሺህ ቤት ፈላጊዎች ቤት እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፥ ቤት ፈላጊዎችን የማደራጀቱ ሂደት ግን ተቋርጦ እንደነበር ገልፀዋል።

በዚህ አመት ቤት ፈላጊዎችን ለማደራጀት እና ምዝገባ ለማከናወን ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።

ኮሚቴው ቤት ፈላጊዎቹን የማደራጀት፣ የመመዝገብ እንዲሁም የቤት ፈላጊውን እና የከተማዋን የማስተናገድ አቅም የመለየት ስራ ይሰራል ተብሏል።

በድጋሚ ሊከናወን በታሰበው የቤት ልማት መርሀ ግብርም ከዚህ ቀደም የተደራጁ ቤት ፈላጊዎችን ጨምሮ አዲስ የሚመዘገቡትን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚሰራ ተገልጿል።

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.