Fana: At a Speed of Life!

በጥገና ምክንያት ከጢስ አባይ ፏፏቴ ግርጌ የሚገኙ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥገና ምክንያት ከጢስ አባይ ፏፏቴ ግርጌ የሚገኙ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳሰበ።

በጢስ አባይ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሚካሄደው ጥገና ምክንያት የጢስ አባይ ፏፏቴ ውሃ ከነገ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መጠኑን ጨምሮ ይለቀቃል ብሏል በማሳሰቢያው።

ስለሆነም ከፏፏቴው ግርጌ በሚገኙ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ነው ያለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.