Fana: At a Speed of Life!

የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግንባታ አፈፃፀም 80 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግንባታ አፈፃፀም 80 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ ለማምረቻ ኢንዱስትሪ አስፈላጊ የሆኑ የመሰረተልማቶች እየተሟላለት ሲሆን በሚቀጥሉት ቅርብ ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ባለሀብቶችን ለመሳብ ዝግጁ ይሆናል፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰመስተዳድር አቶ አወል አርባ፥ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፥ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚሚ እና የኮርፖሬሽኑ የልማት ዘርፍ የስራ ሀላፊዎች የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክን የግንባታ ደረጃ የመስክ ግምገማ አካሂደዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ 80 በመቶ በላይ የግንባታ አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የመጨረሻ የግንባታ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

ፓርኩ ሀገሪቱ እየተገለገለችበት ከምትገኘው የጁቡቲ ወደብ እና ሌሎች በአቅራቢያ ለሚገኙ ወደቦች በቅርብ ርቀት መገኘቱ በወጪ ንግድ ዘርፍ ለሚሰማሩ አምራቾች ሳቢ ያደርገዋል፡፡

የፓርኩ የመጀመርያ ምዕራፍ ግንባታ በ50 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በውስጡ ስምንት ባለ 5 ሺህ 500 ካ.ሜ የማምረቻ ህንፃዎችን ይዟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.