የሀገር ውስጥ ዜና

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 2 ሺህ 93 ተማሪዎችን አስመረቀ

By Tibebu Kebede

March 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 93 ተማሪዎች አስመረቀ።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የፖለቲካና የሲቪክ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አለሙ ስሜ ተመራቂዎች በሰለጠኑበት ሙያ ለሀገራቸው ብልፅግና እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ በቀጣይ የምታከናውነው ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ ይጠናቀቅ ዘንድ ተመራቂዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጎን ለጎን በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ መሠማራቱን ገልፀዋል፡፡

ለዚህም ለማህበረሰቡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ድምፃዊ አሊ ቢራን ጨምሮ ለበርካቶች የክብር ዶክትሬት መስጠቱን ለአብነት አንስተዋል።

የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎችም በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!