Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ ከተማ የካናቢስ እፅና ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምግቦችና መጠጦች ተወገዱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዋሳ  ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት  በስሩ  ከሚገኙ ስምንት ኬላ ጣቢዎች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ  በቁጥጥር  ስር ያዋለውን  የካናቢስ ዕፅ በትላንትናው እለት አስወግዷል ።

ከካናቢስ ዕፁ በተጨማሪ ወደ ሃገር እንዳይገቡ የተከለከሉ ልባሽ ጨርቆች፣ ጫማዎች ፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸው እሽግ ምግቦችና ሽሻዎች እንደሚገኙበት  በፅህፈት ቤቱ  የህግ ተገዢነት ምክትል ስራ አስኪያጅ  አቶ ኢዴሳ ለማ  ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት  ገልፀዋል።

በመሃል አገር ወደ ውጪ ሊወጣ  ሲል የተያዘው የካናቢስ እፅ በኬኒያ ገበያ ላይ ሊውል  እንደነበረ  የገለፁት  ምክትል ስራ  አስኪያጁ   የእፅ ምርቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣት አሳሳቢነው ብለዋል ።

እርቀት ላይ ያሉና  ተራራማ ቦታዎች ለእፅ ምርቱ  መመረጣቸው በሰብል ውስጥ የሚደረገውን ቁጥጥር አስቸጋሪ እንዳደረገውም ጠቁመዋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን  ሀዋሳ  ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር በሚገኙ  ስምንት ኬላዎች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ   የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው መጨመሩንና ቁጥጥሩም መጥበቁን  አመላካች እንደሆነ አቶ ኢዴሳ ለማ ተናግረዋል።

ይህን የሃገር ጉዳት የሆነውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ለመግታት ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት ወገናዊ ትብብሩን ይወጣ ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በመቅደስ አሰፋው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.