ቢዝነስ

የኢትዮጵያ የጫካ ቡናን የተመለከተ ሴሚናር በጃፓን ተካሄደ

By Tibebu Kebede

January 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የጫካ ቡናን የተመለከተ ሴሚናር በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተካሄደ።

በሴሚናሩ የኢትዮጵያ ጫካ ቡናን የተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሁፎች ቀርበው ገለጻ ተደርጓል።

የሴሚናሩ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ የጫካ ቡናን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።

በሴሚናሩ ላይ የኢትዮጵያን ባህላዊ ቡና ማፍላት ስነ ስርዓት በማካሄድ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን የጫካ ቡና እንዲቀምሱ መደረጉም ነው የተገለጸው።

በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሴሚናሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ትልቅ ሚና ለነበራቸው ለአፍሪካ ሪካይ ፕሮጀክትና ለጃፓን የዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ምስጋና ማቅረቡን በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።