ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጎርጎራ ፕሮጀክትን አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለሀገር መርሐ ግብር የሚለማውን የጎርጎራ ፕሮጀክትን የመጀመሪያውን ምዕራፍ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።
በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባደረጉት ንግግር÷ ጎርጎራ የባህርዳር እና የጎንደር የቃልኪዳን ቀለበት የትስስር ማዕከል ናት ብለዋል ።
የጣና ዳር ሀብትን ጠበቅው ላቆዩ አካላት ምስጋና ያቀረቡት ዶክተር ዐብይ በዚህ መልክ መጠበቁ ከማልማት በላይ ነውም ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የኢትዮጵያ ብልፅግና ህልም አይደለም የሚዳስስ እና የሚጨበጥ ተግባር የሚሰራ ነው ብለዋል።
በሶስት ክልሎች ለሚሰሩ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ከ 4 ቢሊየን ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን÷ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ለመጠናቀቅ ይሰራል ተብሏል።
በስነስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በዓላዛር ታደለ እና በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/…/www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!