የሀገር ውስጥ ዜና

የበለስ ጃዊ የሀይል ማከፋፈያና ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ

By Tibebu Kebede

March 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ387 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው በአማራ ክልል አዊ ብሄረሠብ አስተዳደር ዞን የሚገኘው የበለስ ጃዊ የሀይል ማከፋፈያና ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡

61 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ፕሮጀክት ግዙፉን የበለስ ስኳር ፋብሪካ ሀይል የሚመግብ ነው መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሀይል ማከፋፈያ ጣቢያው ከበለስ ስኳር ፋብሪካ በተጨማሪ የጃዊ ከተማን የሀይል ፍላጎት እና ለወደፊት በአካባቢው እምቅ የግብርና ሀብት የሚያለሙ ግዙፍ ፋብሪካዎችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ሞገስ መኮንን ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን፥ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ሚኒስትሮችና የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!