Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥባቸው ጣቢያዎች ምልከታ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ41 የመፈተኛ ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ምልከታ አደረጉ፡፡

በምልከታቸው ፈተናውን በመውሰድ ላይ የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡

ከትምህርት ሚኒስትሩ ጋር ዶክተር ዴላሞ ኦቶሬ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ኃላፊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት የከንቲባዋ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪው አቶ ጥላሁን ፍቃዱ እና አቶ ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች ላይ ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.